am_tn/ezk/01/15.md

1.3 KiB

የመንኩራኩሮቹ ገጽታና መዋቅር ይህንን ይመስል ነበር

“የመንኩራኩሮቹ መልክና አሠራር ይህንን ይመስል ነበር”

እንደ ቢረሌ

ቢረሌ በአብዛኛው ቢጫ ወይም ወርቃማ ቀለም ያለው ንጹሕ የከበረ የድንጋይ ዓይነት ነው። “እንደ ቢረሌ ድንጋይ ንጹሕና ቢጫ” ወይም “እንደ ከበረ ድንጋይ ንጹሕና ቢጫ”

አራቱም ተመሳሳይ መልክ ነበራቸው

እዚህ ጋ፣ የነገር ስም የሆነው “መልክ” አራቱ መንኩራኩሮች ምን ይመስሉ እንደነበር ያመለክታል። ቃሉ ከግሣዊ ሐረግ ጋር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አራቱም መንኩራኩሮች ይመሳሰሉ ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ገጽታቸውና አሠራራቸው አንዱ መንኩራኩር ከሌላው መንኩራኩር ጋር ተላልፎ የተያዘ ይመስል ነበር

“ገጽታ” እና “አሠራር” የሚሉት የነገር ስሞች እንደ ግሥ ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “አንደኛው መንኩራኩር በሌላኛው መንኩራኩር ውስጥ አልፎ የተሠራ ይመስል ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)