am_tn/ezk/01/10.md

1.9 KiB

የፊታቸው መልክ የሰውን ፊት ይመስል ነበር

ሕዝቅኤል የፍጡራኑን የፊት ለፊት ገጽታቸውን ይገልጻል። የነገር ስም የሆነው “መልክ” ማለት ለሕዝቅኤል የሰው ፊት መስሎ የታየው ነው። ቃሉ ወደ ግሣዊ ሐረግ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የእያንዳንዱ ፍጡር ፊት የሰውን ፊት ይመስል ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

በስተቀኛቸው አራቱም የአንበሳ ፊት ነበራቸው

“በእያንዳንዳቸው ራስ በስተቀኝ ያለው ፊታቸው የአንበሳ ፊት ይመስል ነበር”

በስተግራቸው አራቱም የበሬ ፊት ነበራቸው

“በእያንዳንዳቸው ራስ በስተግራ ያለው ፊታቸው የበሬ ፊት ይመስል ነበር”

አራቱም የንስር ፊት ደግሞ ነበራቸው

“በእያንዳንዳቸው ራስ በስተኋላ ያለው ፊታቸው የንስርን ፊት ይመስል ነበር”

እያንዳንዱ ፍጡር የሌላውን ፍጡር ክንፍ የሚነኩ ጥንድ ክንፎች ነበሩት፣ ክንፎቻቸው ወደ ላይ ተዘርግቶ ነበር

“እያንዳንዱ ፍጡር ሁለት ክንፎች ነበሩት፣ አንደኛው ክንፉ በአንድ በኩል ያለውን ፍጡር ክንፍ ይነካ ነበር፣ ሌላኛው ክንፉ በሌላ በኩል ያለውን ፍጡር ክንፍ ይነካ ነበር”

ደግሞም በጥንድ ክንፎቻቸው አካላቸውን ይሸፍኑ ነበር

ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር መተርጎም ይችላል። “የእያንዳንዱ ፍጡር ሁለት ክንፎቻቸው አካሉን ይሸፍኑት ነበር”

እያንዳንዱ ወደ ፊት ቀጥ ብሎ ይሄድ ነበር

“እያንዳንዱ ፍጡር ወደ ፊት እያየ ይጓዝ ነበር”