am_tn/ezk/01/04.md

2.5 KiB

ዐውሎ ንፋስ

ይህ ከፍተኛ የንፋስ ግፊት ያለበት ዐውሎ ነው።

ከሰሜን ይመጣ ነበር

ሰሜን ማለት ፀሐይ ስትወጣ በምታያት ጊዜ በስተግራህ ያለ አቅጣጫ ማለት ነው።

በውስጡ እሳት የሚነድበት ታላቅ ደመና

ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል። “ዐውሎው በውስጡ እሳት የሚነድበት በጣም ታላቅ ደመና ነበረው”

እሳት የሚነድበት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “የመብረቅ ብልጭታ” ወይም 2) “የማያቋርጥ መብረቅ” የሚሉት ናቸው።

ብሩህነት ዙሪያውን ከቦት እና ውስጡን ሞልቶት

“በጣም ብሩህ የሆነ ብርሃን በደመናው ዙሪያና በውስጡም ነበር”

የሙጫ መልክ

“እንደ ሙጫ ያለ ብሩህ ቢጫ” ወይም “ብሩህ ቢጫ” ወይም “ደማቅ ቢጫ”

ሙጫ

ጌጣ ጌጥን ለማስዋብ ጥቅም ላይ የሚውል ደማቅ ቢጫ ሙጫ

በመካከል

“በዐውሎው መካከል”

የአራት ሕያው ፍጡር አምሳያ

እዚህ ጋ የነገር ስም የሆነው “አምሳያ” ትርጉሙ ሕዝቅኤል ያያቸውን እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮችን የሚመስሉትን ነው። ቃሉ ከግሣዊ ሐረግ ጋር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አራት ሕያዋን ፍጡራንን የሚመስሉ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

መልካቸው ይህንን ይመስል ነበር

የነገር ስም የሆነው “መልክ” እንደ ግሣዊ ሐረግ ሆኖ መተርጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይህንን ይመስሉ ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

የሰው መልክ ነበራቸው

የነገር ስም የሆነው “መልክ” እንደ ግሣዊ ሐረግ ሆኖ መተርጎም ይችላል። አ.ት፡ “አራቱ ፍጡራን ሰዎችን ይመስሉ ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ሆኖም እያንዳንዳቸው አራት ፊት ነበራቸው፣ ለእያንዳንዱ ፍጡርም አራት ክንፍ ነበራቸው

“ሆኖም እያንዳንዳቸው አራት የተለያየ ፊትና አራት ክንፍ ነበራቸው”። እያንዳንዱ ፍጡር በፊት ለፊቱ፣ በስተኋላውና ከራሱ ሁለት ወገን ላይ ፊት ነበረው።