am_tn/ezk/01/01.md

3.3 KiB

በሠላሳኛው ዓመት

ይህ የሕዝቅኤል ሠላሳኛው ዕድሜ ነው። (ደረጃን የሚያሳይ ቁጥር የሚለውን ተመልከት)

አራተኛው ወር፣ የወሩም አምስተኛው ቀን

“የአራተኛው ወር አምስተኛው ቀን”። ይህ በዕብራውያን የቀን አቆጣጠር አራተኛው ወር ነው። በምዕራባውያኑ አቆጣጠር አምስተኛው ቀን የሰኔ ወር መጨረሻ አካባቢ ነው። (የዕብራውያን ወራት እና ደረጃን የሚያሳይ ቁጥር የሚለውን ተመልከት)

እንዲህ ሆነ

እዚህ ጋ ይህ ሐረግ ጥቅም ላይ የዋለው በታሪኩ ውስጥ አስፈላጊ የሆነውን ሁነት ለማመላከት ነው። የአንተ ቋንቋ ይህንን የሚያደርግበት መንገድ ካለው እዚህ ጋ መጠቀም እንደምትችል አስብ።

በምርኮኞቹ መካከል እኖር ነበር

“እኔ” የሚለው ቃል ሕዝቅኤልን ያመለክታል። “እኔ ከምርኮኞቹ አንዱ ነበርኩኝ”

የእግዚአብሔርን ራዕዮች አየሁ

“እግዚአብሔር ያልተለመዱ ነገሮችን አሳየኝ”

ንጉሡ ዮአኪን የተማረከበት አምስተኛ ዓመት ነበር

በመጽሐፉ ሁሉ፣ ሕዝቅኤል ትንቢቶቹን መናገር የሚጀምረው ዮአኪን ኢየሩሳሌምን ለቆ እንዲሄድ ባቢሎናውያን ካስገደዱት ጊዜ ጀምሮ ነው።

ወደ ሕዝቅኤል … በዚያ በእርሱ ላይ

ሕዝቅኤል ሌላ ሰው ይመስል ስለ ራሱ ይናገራል። አ.ት፡ “ወደ እኔ ወደ ሕዝቅኤል … በዚያ በእኔ ላይ” (ተውላጸ ስም የሚለውን ተመልከት)

የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሕዝቅኤል መጣ

“የእግዚአብሔር ቃል ወደ -- መጣ” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ጥቅም ላይ የዋለው ከእግዚአብሔር የመጣውን ልዩ መልዕክት ለማሳወቅ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ለሕዝቅኤል መልዕክት ሰጠው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ቡዝ

የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

የኮቦር ቦይ

ይህ ከለዳውያን የአትክልት ቦታቸውን ለማጠጣት የቆፈሩት ወንዝ ነው። “የኮቦር ወንዝ”

የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረች

አብዛኛውን ጊዜ “እጅ” ጥቅም ላይ የዋለው የአንድን ሰው ኃይል ወይም ተግባር ለማመልከት ነው። አንድ ሰው እጁን በሌላው ላይ ሲያደርግ፣ በዚያ ሰው ላይ ኃይል ይኖረዋል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እየተቆጣጠረው ነበር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ያህዌ

ይህ በብሉይ ኪዳን ራሱን ለሕዝቡ የገለጠበት የእግዚአብሔር ስም ነው። ይህንን እንዴት መተርጎም እንደሚኖርብህ ለማወቅ ስለ እግዚአብሔር የቃል ገጽን ትርጉም ተመልከት።