am_tn/exo/39/32.md

1.4 KiB

አጠቃላይ ምልከታ፦

በምዕራፍ 35፡4-9 እና 35፡10-12 ላይ በተሰጠው መመሪያ መሰረት እስራኤላውያን የተሰጣቸውን ሥራ ሲጨርሱ ያሳየናል።

• እንዲሁም የመገናኛው ድንኳን የማደሪያውም ሥራ ሁሉ ተጨረሰ

ይህ በተደራጊ ግስ የተገለጸው ዐረፍተ ነገር “የእስራኤል ልጆች የመገናኛውን ድንኳን ሥራውን ሁሉ ጨረሱ” በሚለው ልተረጎም ይችላል። “የመገናኛው ድንኳን የማደሪያውም” የሚሉ ቃላት ሁለቱም ስለአንድ ነገር የሚያወሩ ናቸው።

• የማደሪያውን ድንኳን ወደ ሙሴ አመጡት

የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሰረት የተሰራውን የመገናኛውን ድንኳን ወደ ሙሴ አመጡ ማለት ነው።

• መያዣዎች

መጋረጃዎችን በአንድ ለማያያዝ የሚጠቅሙ ነገሮች ወይም አቃፊዎች ናቸው። ዘጸአት 26፡4-6 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት።

• እግሮቹንም

ምሶሶዎች የሚቆሙባቸው እግሮች ማለት ነው።

• የስርየት መክደኛውንም

ከታቦቱ ላይ የሚቀመጥ መሸፈፍኛ ወይም መክደኛ ሲሆን የስርየት መስዋዕት የሚቀርብበትም ጭምር ነው።