አጠቃላይ ምልከታ፦
በምዕራፍ 28፡34-35 ላይ በተሰጠው መመሪያ መሰረት በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
• ከጥሩ ወርቅም ሻኵራዎችን
ከጥሩ ወርቅ ጸናጽሎችን ወይም ትናንሽ ድምጽ የሚሰጡ ቁርጥራጭ ነገሮችን ማለት ነው።
• ሻኵራንና ሮማንን፥ ሻኵራንና ሮማንን ለማገልገል አደረጉ
በአገልግሎት ወቅት እንዲለብሱ ጸናጽሎችንና ሮማን ፍሬ መሳይ ስዕሎችን በቀሚሱ ጠርዝ ወይም ጫፍ ዙሪያ አደረጉ