am_tn/exo/39/10.md

1.1 KiB

አጠቃላይ ምልከታ፦

በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል

• ዕንቁዎቹንም በአራት ተራ አደረጉበት

ሠራተኞች የከበሩ ድንጋዮችን በተነገራቸው መሰረት በአራት ረድፍ አደርገው ሰሩት

• ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን …

የአነዚህን ድንጋዮች ስም ዝርዝር በየቋንቋው ለማግኘት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ዕንቁ የተባሉት “የከበሩ ወይም ውድ” የድንጋይ ዓይነቶች መሆናቸውና አንዱ ከሌላው የተለየ መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ስለሆነም በትርጉም ወቅት ተውሶ ወይም ባዕድ ቃላትን በመጠቀም ትርጉሙን ግልጽ ማድረግ ይቻላል።

• በወርቅ ፈርጥ ተደረጉ

እነዚህን የከበሩ ወይም ውድ ድንጋዮችን በወርቅ ፈርጥ ወይም በተቀረጸው ወርቅ ላይ አስቀመጡ