am_tn/exo/37/17.md

1.0 KiB

አጠቃላይ ምልከታ፦

ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የማደሪያውን ድንኳንና በውስጡ የሚገኙ ሥራዎችን ስለመሥራታቸው ምዕራፍ 37፡17-19 ያለውን ክፍል ከምዕራፍ 25፡31-33 ካለው ጋር በማነጻጸር ተገቢውን የትርጉም ሂደት በመከተል መልዕክቱን ለመተርጉም ሞክር።

• ጽዋዎቹን፥ ጕብጕቦቹን፥ አበቦቹን ከዚያው በአንድነት አደረገ

የአበባ ቅርጽ ያላቸው ጽዋዎችን፥ እንቡጦችንና የፈኩ አበቦችን አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው

• ጕብጕቡንና አበባውን ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች

ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሶስት ጽዋዎች

• የለውዝ አበባ

ነጭ ወይም ሮዝ መልክ ያለው የለውዝ አበባ በለውዝ ዘፍ ላይ ያደገ የሚመስል ነበር