957 B
957 B
አጠቃላይ ምልከታ፦
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የማደሪያውን ድንኳንና በውስጡ የሚገኙ ሥራዎችን ስለመሥራታቸው ምዕራፍ 37፡10-13 ያለውን ክፍል ከምዕራፍ 25፡23-26 ካለው ክፍል ጋር በማነጻጸር በተገቢው መንገድ ለመተርጎም ሞክር።
• ርዝመቱ ሁለት ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል
ርዝመቱ 92 ሴ.ሜትር፤ ወርዱ 46 ሴ.ሜትር እና ቁመቱ 69 ሴ.ሜትር ያህል ነበር
• አንድ ጋት
በባህላዊው ልከት አንድ ጋት የአራት ጣቶች ጥምር ማለት ሲሆን ከ8-10 ሳ.ሜትር ነው።
• አራቱ እግሮቹ
እነዚህ እግሮች እንደሰው ወይም እንስሳ እግር የተቆጠሩ ሲሆን ታቦቱን የሚሸከሙ ወይም የሚደግፉ ናቸው።