am_tn/exo/34/21.md

931 B

አጠቃላይ ምልከታ፦

እግዚአብሔር (ያህዌ) እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው በሙሴ በኩል ያሳስባቸዋል።

• በምታርስበትና በምታጭድበት ዘመን ታርፋለህ

“በእርሻም ወቅትም ሆነ በመከር ወቅት በሰባተኛው ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ” ወይም “በእርሻና በመከር ጊዜ እንኳ ቢሆን ማረፍ አለብህ”

• የመክተቻ በዓል

ይህ በዓል የዳስ በመባል ይታወቃል። ይህ ልምምድ የመጣው እርሻቸውን በዳስ ወይም በጊዜያዊ ጎጆ ውስጥ ሆነው ያረሱና እህሉ እስኪደርስ ድረስ በዚያ ዳስ ሆነው ከአውሬ ሲጠብቁ የነበሩ አርሶ አደሮች ልምምድ ነው። “መክተቻ” የተባለው የእህል ማከማቻ ማለት ነው።