am_tn/exo/34/08.md

1.5 KiB

• በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ

በዚህ ሀረግ “ሞገስ አግኝቼ” የሚለው የሚያመለክተው ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ዕውቅና ያገኘ ወይም እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ ደስ ተሰኘ ማለት ነው። “በፊትህ” የተባለው በእግዚአብሔር እይታ ወይም የእግዚአብሔርን ግምገማ የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ አንተን ገምግሜ ዕውቅና ሰጥቼሃለሁ፤ ወይም በአንተ ተደስቻለሁ/በአንተ ደስ ይለኛል/

• ክፋታችንንና ኀጢአታችንን ይቅር በል

ሁለቱ ቃላት የፍች ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም ልዩነት በመካከላቸው እንዳለ እሙን ነው። እዚህ ጋር በአንድ ላይ የመጡበት ምክንያት አጽንኦት ለመስጠት ነው። ሁለቱን ቃላት ለየብቻ ለመተርጎም የማይቻል ከሆነ ሀጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን ማለት ይቻላል።

• እንደ ርስትህም አድርገህ ውሰደን

ይህ አነጋገር አንድ ሰው አንድን ንብረት ካለበት ቦታ እንደሚወስድ ዓይነት አነጋገር ርስትህ አድርገህ ውሰደን ይላል። አማራጭ ትርጉም፦ የራስህ ሕዝብ አድርገህ ተቀበለን ወይም እኛን ህዝብህን እንደ ርስትህ የራስህ አድርገህ ተቀበለን