am_tn/exo/34/05.md

2.1 KiB

• በዚያም ከእርሱ ጋር ቆመ

“እግዚአብሔር በተራራው ላይ ከሙሴ ጋር ቆመ”

• የእግዚአብሔርንም ስም አወጀ

የዚህ ዐረፍተ ነገር ፍቺ 1) እርሱ ስሙን እግዚአብሔር (ያህዌ) ብሎ ተናገረ 2) እርሱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ማን እንደሆነ ተናገረ። ስሙ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ አመልካች ነውና።

• እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው

እግዚአብሔር ስለራሱ ይናገራል፤ አማራጭ ትርጉም፦ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ርህሩህና መሐሪ አምላክ ነኝ

• ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት

ይህ አባባል በተለያዩ ቅጂዎች በሁለት መንገድ ይታያል። አንዳንድ ቅጂዎች በአንደኛ መደብ ሲንገሩ ሌሎች በ3ኛ መደብ ይናገራል። ስለዚህ በሁለቱም ትክክል ናቸው፤ 1) እኔ ለቊጣ የዘገየሁ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅሬና ታማኝነቴ የበዛ ነው 2) እግዚአብሔር (ያህዌ) ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ ነው

• እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ

ቃል ኪዳኔን እስከ ሽህ ትውልድ ድረስ እጠብቃለሁ ወይም ዘለዓለማዊ ፍቅሬንም እስከ ብዙ ሺህ ትውልድ እጠብቃለሁ

• በደለኛውን ግን ሳይቀጣ ዝም ብሎ አይተውም

በሶስተኛ መደብ የተነገረው እግዚአብሔር ራሱን በሶስተኛ መደብ ሲናገር ይታያል። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ እግዚአብሔር ሀጢአተኛውን/በደለኛውን ሳልቀጣ አልተውም

• በአባቶች ኀጢአት ልጆችን የልጅ ልጆቻቸውን እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ይቀጣል

በአባቶች ሀጢአት ምክንያት ልጆቻችሁንና ልጅ ልጆቻችሁን እስከ ሶስትና አራት ትውልድ ድረስ እቀጣለሁ