am_tn/exo/33/12.md

1.5 KiB

• እነሆ

“እይ” ወይም “ስማ” ወይም “አድምጠኝ” እንደማለት ነው። ቃሉ በዕብራይስጥ ትኩረት ለመሳብ ወይም የሀሳብ አንድነት መኖሩን ለማመልከት የገባ ነው።

• በስምህ አወቅሁህ

አንድን ሰው በስም ማወቅ ያንን ሰው በሚገባ ወይም በትክክል እናውቄዋለን ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “እኔ አንተን በደንብ አውቅሃለሁ”

• በእኔ ፊት ሞገስን አገኘህ (ዘይቤያዊ አነጋገር)

በዚህ ሀረግ “ሞገስ አገኘህ” የሚለው የሚያመለክተው ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ዕውቅና ያገኘ ወይም እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ ደስ ተሰኘ ማለት ነው። “እኔ ፊት” የተባለው በእግዚአብሔር እይታ ወይም የእግዚአብሔርን ግምገማ የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ አንተን ገምግሜ ዕውቅና ሰጥቼሃለሁ ወይም በአንተ ተደስቻለሁ/በአንተ ደስ ይለኛል/

• መንገድህን እባክህ አሳየኝ

ይህን ሀረግ በሁለት መልኩ መተርጎም ይቻላል፦ ወደፊት ማድረግ የምትፈልገውን ነገር እባክህ ንገረኝ ወይም ወደፊት ህዝቡ ማድረግ የሚገባቸውን ነገር እባክህ አሳያቸው