am_tn/exo/33/01.md

1.7 KiB

አጠቃላይ ምልከታ፦

ምልከታ፦ እግዚአብሔር (ያህዌ) በህዝቡ ላይ መቆጣቱን ቀጥሎ ይናገራል።

• ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው ምድር

ይህ ሐረግ በግነታዊ እና በተለዋጭ ዘይቤ የተገለጸ ነው። ይህ አገላለጽ ከምድሪቱ ወተትና ማር ይፈልቃል ማለት ሳይሆን ለከብት እርባታና ለእርሻ በጣም ምቹ የሆነ ምድር እንደሆነ ለማሳየት ነው። እንዲሁም “የምታፈስ” አገር የሚለው ቃልም ሁሉም ነገር የሞላባት ምድር የሚል ፍቺ ያለው ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ለከብት እርባታና ለእርሻ ምቹ የሆነ ምድር

• ወተት

በእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ የዳበረች አገር መሆኑዋን ለማመልከት ነው

• ማር

በእስራኤል ምድር ማር በሁለት መንገዶች ይመረታል። አንደኛው ከንብ እርባታ የሚገኘው ሲሆን ሁለተኛው ከተምር ዛፍና ከሌሎች ዕጽዋት የሚገኘው ነው።

• አንገተ ደንዳና ሕዝብ

ጸሐፊው የማይታዛዝ ህዝብ መሆኑን ለማሳየት በዘይቤያዊ አነጋገር ይገልጻል። የልባቸው እልከኝነት ከአንገት ደንዳናነት ጋር ተነጻጽሯል። አንገተ ዳንዳና ማለት ገታራና የማይመለስ ወይም መታጠፍ የማይችል ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ የማይሰማና የማይታዘዝ ህዝብ፤ ለለውጥ ያልተዘጋጀ ህዝብ ወይም ከገታራ አቋሙ የማይመለስ ማለት ነው።