1.4 KiB
1.4 KiB
• እርሱን ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ
“እርሱን” የሚለው ያንን ሀጢአት የሰራውን ሰው ስም ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔን የበደለኝን ሰው ስም ከመጽሐፌ እሰርዛለሁ
• ከመጽሐፌ
ይህ መጽሐፍ ሙሴ የሚናገረው የእግዚአብሔር (ያህዌ) መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉ ባለበት እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።
• ነገር ግን በምጐበኝበት ቀን ኃጢአታቸውን አመጣባቸዋለሁ አለው
ነገር ግን እኔ እነርሱን የምቀጣበት ጊዜ ሲደርስ ስለ ኀጢአታቸው የምቀጣው እኔ እግዚአብሔር ነኝ
• እግዚአብሔር ሕዝቡን ቀሠፈ
በምን ዓይነት ሁኔታ ህዝቡን እንደቀሰፈ አልተገለጸም ነገር ግን በበሽታ ሊሆን ይችላል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ከባድ በሽታ ላከ
• አሮን የሠራውን ጥጃ ስለ ሠሩ
የጥጃ ምስል ጣኦት የሰራው አሮን ቢሆንም ያንን የጥጃ ምስል ጣኦት አሮን እንዲሰራው ያስገደዱት ህዝቡ ነበሩ። አማራጭ ትርጉም፦ አሮን የጥጃ ምስል ጣኦት እንዲሰራ ህዝቡ በማስገደዳቸው