am_tn/exo/32/21.md

2.0 KiB

• ይህን ታላቅ ኃጢአት ታመጣበት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደረገህ? (ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ጥያቄ)

“ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ወይም በድሎህ ነው ይህን የመሰለ ክፉ ኃጢአት እንዲሠራ ያደረግኸው?”

• ይህን ታላቅ ኃጢአት ታመጣበት ዘንድ

ሀጢአት እንደ አንድ ግዑዝ ነገር ሆኖ አሮን በህዝቡ ላይ እንዳመጣበት በዘይቤያዊ አነጋገር ሙሴ ይገልጸዋል። አማራጭ ትርጉም፦ ይህን ክፉ ሀጢአት እንዲሰሩ ምክንያት የሆንከው አሮን አንተ ነህ

• ጌታዬ ሆይ፥ ቁጣህ አይቃጠል (ዘይቤያዊ አነጋገር)

ጌታዬ በእኔ ላይ እንዲህ በሀይል አትቈጣ

• ይህ ሕዝብ ክፋትን እንዲወድድ አንተ ታውቃለህ (ዘይቤያዊ ንግግር)

ይህ ሕዝብ ምን ያህል የክፋት ዝንባሌ እንዳለው ወይም ክፉ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው አንተ ታውቃለህ

• ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ

“ይህ ሙሴ” የሚለው ሀረግ ህዝቡ ለሙሴ ያለው አክብሮት እንደ ወረደባቸው የሚገልጽ ነው። ከዚህ በፊት ሙሴን እንደማያውቁና እርሱም የማይታመን ሰው እንደሆነ “ይህ ሙሴ” በሚለው ሀረግ አርቀው ይናገራሉ።

• እኔም፦ ከእናንተ ወርቅ ያለው ሰው ከእርሱ ሰብሮ ያምጣልኝ

እኔ የወርቅ ጉትቻዎቻቸውን ወይም ጌጣጌጦቻቸውን አውልቀው ወይም ሰብረው እንዲያመጡልኝ ነገርኳቸው

• በእሳትም ላይ ጣልሁት፥ ይህም ጥጃ ወጣ

አሮን ሀላፊነት የወርቅ ጥጃውን ስለመስራቱ ላለመውሰድ ሲፈልግ እኔ ወርቆቹን ወደ እሳት ጣልኩኝ ነገር ግን ይህ ጥጃ ወጣ ብሎ ሲያስተባብል እናያለን።