• እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ
ይህ በዘይቤያዊ አነጋገር የተገለጸ ሲሆን አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር እንደተገለጠ ወይም እንደታዬ አድርጎ ተገልጿል። አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ ዘገየ በተረዱ ወይም ባስተዋሉ ጊዜ”
• ወደ አሮን ተሰብስበው
አሮንን አንድ ጥያቄ ለመጠየቅና ለማስገደድ እንደ መጡ ያሳያል። አማራጭ ትርጉም፦ ወደ አሮን መጥተው ወይም ቀርበው
• በፊታችን የሚሄዱ
እኛን የሚመሩን ወይም መሪ ልሆኑን የሚችሉ