1.8 KiB
1.8 KiB
• ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ
እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን የሚነግራቸው የሰንበት ቀን በማክበር እርሱን እንድታዘዙ ነው።አማራጭ ትርጉም፦ “የሰንበት ቀን በማክበር እኔን መታዘዝ አለባችሁ”
• በእኔና በእናንተ ዘንድ ለልጅ ልጃችሁ ምልክት ነው
ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ወይም እስከ ልጅ ልጃችሁ ድረስ ምልክት ይሆናል
• እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ
እግዚአብሔር ለራሱ የለያችሁ ወይም የመረጣችሁ ሰዎች ናችሁ
• ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ
የሰንበት ቀን ማክበር ቅዱስ ተግባር ስለሆነ ሰንበቴን አክብሩ
• የሚያረክሰውም ሰው
ሰንበትን ማክበር የማይፈልግ ወይም የሰንበት ቀን አክብሮት የሚሽር ሰው ወይም ትኩረት የማይሰጥና የሚንቅ ሰው
• ሁሉ ፈጽሞ ይገደል
በአድራጊ ግስ፦ ይህን ሰው ግደሉ ወይም ከመካከላችሁ አስወግዱ ወይም ይህ ሰው በሞት ይቀጣ
ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ
ይህ አባባል በተለያዩ መንገዶች ልተረጎም ይችላል
- እግዚአብሔር ይህን ሰው ከህዝቡ መካከል ይለየዋል ወይም እንደራሱ ህዝብ አይቆጥረውም
- እናንተ እስራኤላውያን ይህን ሰው ከመካከላችሁ ለዩ ወይም አስወግዱ
- እናንተ እስራኤላውያን ይህን ሰው ያለ ርህራሄ ግደሉት
• ሰባተኛው ቀን
ቀን 7 ወይም የሳምንቱ 7ኛ ቀን