1.3 KiB
1.3 KiB
አጠቃላይ ዕይታ፦
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
• ቅመም
ጥሩ ሽታና ጣዕም እንዲኖረው ከደረቀ ዕጽዋትና ዘር ተፈጭቶ የተሰራና ዘይት ወይም ምግብ የገባበት ዱቀት ነክ ነገር ነው (ዘጸአት 25፡6 ተመልከት)
• አምስት መቶ ሰቅል . . . ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል . . . ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥
አንድ ሰቅል 11 ግራም ሲሆን ተርጓሚዎች ማህበረሰቡ በየዕለቱ አገልግሎቱ የምጠቀምበትን መለኪያ መጠቀም የተሻለ ነው። 500 ሰቅል ----- 5.5 ኪሎ ግራም፤ 250 ሰቅል ---- 2.75 ኪሎ ግራም፤ 250 ሰቅል ---- 2.75 ኪሎ ግራም ሲሆን በጠቅላላው 11 ኪሎ ግራም ያህል ነው።
• ጣፋጭ ቀረፋ
ጣፋጭ ሽታ ያለው ቀረፋ (የቅመም ዓይነት)
• እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን
በጊዜው ወይም በዚያን ጊዜ ሁለት ዓይነት ሚዛን እንዳለ ይታወቃል፤ አንደኛው መደበኛ የሆነ መገበያያ ሰቅል ሲሆን ሌላኛው ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚሰጥ ሰቅል ነው።