am_tn/exo/29/31.md

1007 B

አጠቃላይ ዕይታ፦

እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል

• የሚካንበትንም አውራ

ለካህናት የአገልግሎት ሹመት/ሥልጣን/ በምትሰጥበት ጊዜ የታረደው የበግ ጠቦት

• በተቀደሰ ስፍራ ትቀቅለዋለህ

ይህ ቦታ ከቅድስተ ቅዱሳን ወጭ ያለው ቅዱስ ስፍራ የሚመለከት አይደለም። ነገር ግን በመገናኛው ደንኳን አደባባይ ላይ ያለውን ሥፍራ የሚመለከት ነው።

• መገናኛው ድንኳን

በሌላ ስሙ የማደሪያ ድንኳን ተብሎ ይታወቃል (ዘጸአት 27፡21 ተመልከት)

• ሌላ ሰው ግን አይብላው

በሌላ አገላለጽ፦ ከካህናት ሌላ ማንም ሰው አይብላው

• የተቀደሰ ነውና

በሌላ አገላለጽ፦ ምክንያቱም የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ነው