1.0 KiB
1.0 KiB
አጠቃላይ ዕይታ፦
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
• በአንድ ሌማትም ታደርጋቸዋለህ
“ሌማት” የተባለው የዳቦ/የቂጣ/የእንጀራ/ ወይም ሌላ ምግብ ማስቀመጫ የሚያመለክት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ሁሉንም በመሶብ ወይም በቅርጫት መሳይ ነገር ታስቀምጣቸዋለህ/ ታኖራቸዋለህ/
• ከወይፈኑና ከሁለቱ አውራ በጎች ጋር በሌማቱ ታቀርባቸዋለህ
በዚህ ክፍል “ታቀርባቸዋለህ” የሚለው መስዋዕት ማቅረብን የሚመለከት ነው። በሌላ አገላለጽ፦ አንድ ኰርማ/ወይፈን/ እና ሁለቱን አውራ በጎች በምትሠዋበት ጊዜ ለእኔ መባ/መስዋዕት/ አድርገህ አቅርብልኝ/ሰዋልኝ/
• መገናኛው ድንኳን
በሌላ ስሙ የማደሪያ ድንኳን ተብሎ ይታወቃል (ዘጸአት 27፡21 ተመልከት)