1.2 KiB
1.2 KiB
አጠቃላይ ምልከታ፦
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
• የአደባባዩ ርዝመት መቶ ክንድ ስፋቱም አምሳ ክንድ ይሁን
የድንኳኑ አደባባይ ርዝመቱ አርባ ስድስት ሜትር የጐኑ ስፋት ሃያ ሶስት ሜትር ሆኖ ይሰራ
• መጋረጃውም ከጥሩ በፍታ
መጋረጃው ከጥሩ /ከቀጭን/ የሐር ጨርቅ/ክር/ የተሰራ ይሁን ወይም መጋረጃውን ከጥሩ/ከቀጭን/ የሐር ጨርቅ/ክር/ ሥራ
• ለማገልገል ሁሉ የማደሪያው ዕቃ ሁሉ፥ ካስማዎቹም ሁሉ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ፥ የናስ ይሁኑ
በድንኳኑ ውስጥ የሚገኙት ለማናቸውም አገልግሎት የሚውሉ የመገልገያ ዕቃዎችን ሁሉ፥ የድንኳኑንና የአደባባዩ ካስማዎችን ሁሉ ከነሐስ ብረት ሥራቸው።
• ካስማዎች
ከብረት ወይም ከእንጨት የተሰሩ በአንድ በኩል ሹል የሆኑ ድንኳን ለመወጠር የሚያገለግሉ ናቸው