905 B
905 B
አጠቃላይ ምልከታ፦
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
• አመድ የሚሆንባቸውን ምንቸቶች
ለዐመድ ማጠራቀሚያነት የሚያገለግሉ ድስቶች /ድስት መሳይ ነገሮች/
• መጫሪያዎች
የእሳት መጫሪያዎች ወይም የእሳት መለኮሻዎች
• ዕቃውንም ሁሉ
በመሰዊያው ላይ ለመጠቀም የሚያገለግሉ ማንኛውንም ቁሳቁስ
• እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የናስ መከታ አድርግለት
እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የነሐስ መከላከያ አብጅለት/ሥራለት/
• የናስ መከታ
እንጨት በእሳት ሲቃጠል ለመያዝ የሚያገለግል ከነሐስ ብረት የተሰራ መያዣ