am_tn/exo/23/26.md

855 B

አጠቃላይ ዕይታ፡-

እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን

• በምድርህም መካን ወይም የምትጨነግፍ አትሆንም

በሌላ አገላለጽ፦ በምድርህ ጽንስ የሚያስወርዳት ወይም መካን ሴት አትኖርም ወይም በምድርህ ያሉ ሴቶች ያረግዛሉ እንዲሁም ይወልዳሉ

• የምትጨነግፍ

ጊዜው ሳይደርስ የምትወልድ እና ልጇ የሚሞትባት ሴት

• በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ

“ተርብ” ሰዎችን በመንደፍ ስቃይ የሚያስከትሉ በራሪ ነፍሳት

• ምድር ባድማ እንዳትሆን

ምድርቱ ሰው የማይኖርባት ምድር እንዳትሆን