am_tn/exo/23/18.md

1.0 KiB

አጠቃላይ ዕይታ፡-

እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን

• የበዓሌም ስብ እስኪነጋ አይደር

ስቡ የሚበላ ሳይሆን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መስዋዕት ሆኖ መቅረብ አለበት። ስለሆነም “ለነገ እንዲያድር አይፈቀድም ወይም እስከ ነገ መቆየት የለበትም”

• የተመረጠውን

ከእርሻ ምርቱ የተሻለውን ወይም መጀመሪያ የደረሰውን”

• ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል

ይህ ድርጊት የከነዓናውያን ልምምድ ሲሆን ምርታማነትን ይጭምራል ተብሎ ስለሚታሰብ የሚደረግ ነው። ስለሆነም እስራኤላውያን ይህንን ድርጊት እንዳያደርጉ ተከልክለዋል። አማራጭ ትርጉም፦ “የበግ ወይም የፍየል ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል”