am_tn/exo/23/16.md

1.0 KiB

አጠቃላይ ዕይታ፡-

እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን

• የመክተቻውን በዓል ጠብቅ

ይህ በዓል የዳስ በመባል ይታወቃል። ይህ ልምምድ የመጣው እርሻቸውን በዳስ ወይም በጊዜያዊ ጎጆ ውስጥ ሆነው ያረሱና እህሉ እስኪደርስ ድረስ በዚያ ዳስ ሆነው ከአውሬ ሲጠብቁ የነበሩ አርሶ አደሮች ልምምድ ነው። “መክተቻ” የተባለው የእህል ማከማቻ ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “በዓመቱ መጨረሻ የዳስ በዓል አክብሩ”

• ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ

እዚህ ቦታ “ይታይ” የሚለው ለአምልኮ መሰብሰብን የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ወንድ ሁሉ እግዚአብሔርን (ያህዌን) ለማምለክ በአንድ ላይ መሰብሰብ አለበት።