am_tn/exo/23/01.md

946 B

አጠቃላይ ዕይታ፡-

እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን

• ሐሰተኛ ምስክርም ትሆን ዘንድ

ተንኰል ያለበትን ምስክርነት በመስጠት ወይም በሀሰት በመመስከር

• ብዙ ሰዎችን አትከተል

ይህ ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን አንድ ሰው ከብዙ ሰው ጋር በመስማማት ፍለጋቸውን መከተልን የሚያመለክት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ክፉ ለማድረግ የተሰባሰቡ ሰዎችን አትከተል ወይም ብዙ ሰዎች የሚፈልጉትን ለማድረግ ከእነርሱ ጋር አትተባበር

• ፍርድንም ለማጥመም

ፍትህን ወይም እውነተኛ ፍርድን ለማዛባት ወይም የህሊና ዳኝነት ለመካድ ወይም ላለመስማት