am_tn/exo/22/01.md

1.7 KiB

አጠቃላይ ዕይታ፦

እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን

• ቢሰርቅ

በሌላ አገላለጽ፦ አንድ ሰው ሌባ ሆኖ ቢገኝ ወይም አንድ ሰው ሰርቆ ቢገኝ

• ሌባው ቤት ሲምስ ቢገኝ

በሌላ አገላለጽ፦ አንድ ሌባ የአንድ ሰው ቤት ሰብሮ ቢገባ

• እርሱም እስኪሞት ቢመታ

በሌላ አገላለጽ፦ አንድ ሰው ቢመታውና ሌባው ቢሞት

• በመታው ሰው ላይ የደም ዕዳ አይሆንበትም

በሌላ አገላለጽ፦ ተከላካዩ ወይም ሌባውን መቶ የገደለው ሰው ለፈሰሰው ደም ወይም በመግደሉ ተጠያቂ አይሆንም

• ፀሐይ ግን ከወጣችበት የደም ዕዳ አለበት

በሌላ አባባል፦ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ወይም ብርሃን እያለ ሌባው ተመትቶ ቢገደል ግን ተከላካዩ በግድያው ተጠያቂ ይሆናል

• ሌባው የሰረቀውን ይመልስ

ሌባው የሰረቀውን መክፈል አለበት ወይም ሌባው በሰረቀው ንብረት ምትክ ክፊያ መስጠት አለበት

• የሚከፍለውም ቢያጣ ስለ ሰረቀው ይሸጥ

ምንም ከሌለው ግን የሰረቀውን ይከፍል ዘንድ ራሱ በባርነት ይሸጥ

• የሰረቀው ደኅና ሆኖ በእጁ ቢገኝ

ሌባው የሰረቀው እንስሳ ሕያው ሆኖ ቢገኝ ወይም በሕይወት ቢገኝ

• የሰረቀውን ያህል ሁለት እጥፍ ይክፈል

ለያንዳንዱ እንስሳ ዕጥፍ ዋጋ ወይም ሁለት እንስሳ ይክፈል