am_tn/exo/21/28.md

1.4 KiB

• በሬ ወንድን ወይም ሴትን . . . ቢወጋ

የአንድ ሰው በሬ አንድን ሰው በቀንዱ ወግቶ ቢገድል

• በሬው ይወገር

በሬው በድንጋይ ተወግሮ ይሙት ወይም በሬውን በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉት

• ሥጋውም አይበላ

በሌላ አገላለጽ፦ የበሬውን ሥጋ አትብሉ ወይም የበሬው ሥጋ አይበላ

• የበሬው ባለቤት ግን ንጹሕ ነው

በሌላ አገላለጽ፦ የበሬው ባለቤት በነጻ ይለቀቅ ወይም የበሬውን ባለቤት በነጻ ልቀቁት አይጠየቅ

• ባለቤቱ ደግሞ ይገደል

የበሬው ባለቤት ወይም ባለ ንብረቱ በሞት ይቀጣ ወይም የበሬውን ባለቤት ወይም ባለ ንብረቱን ግደሉት

• ከእርሱ ግን ካሳ ቢፈልጉ

ተጎጂዎች ካሳ ክፊያ ቢፈልጉ የበሬው ባለቤት ሕይወቱን ለማዳን ቢፈልግ ዳኞች የወሰኑበትን መክፈል አለበት። በትርጉሙ ውስጥ ይህ ግልጽ ሆኖ መታየት አለበት። አማራጭ ትርጉም፦ የበሬው ባለቤት ሕይወቱን ለመዋጀት ወይም ከሞት ለመትረፍ ካሣ እንዲከፍል ከተፈቀደለት ወይም ከተስማሙ ካሣውን በሙሉ መክፈል አለበት።