am_tn/exo/21/22.md

980 B

• ልጁን እስክትጨነግፍ ቢገፉአት ባትጎዳ

ህጻኑን ቢያስወርዳት ወይም ያለጊዜው ተወልዶ ቢሞትና በሴትዮዋ ላይ ሌላ ምንም ጒዳት ሳይደርስ ቢቀር

• የሴቲቱ ባል የጫነበትን ያህል ካሳ ይስጥ

በሌላ አገላለጽ፦ አጥፊው ሰው መቀጣት አለበት ወይም ያጠፋው ሰው ተገቢውን ካሳ መክፈል አለበት

• ፈራጆቹም እንደ ፈረዱበት ይክፈል

ዳኞች የፈረዱበትን ወይም የወሰኑበትን ካሳ መክፈል አለበት

• ጕዳት ግን ቢያገኛት ሕይወት በሕይወት ዓይን በዓይን . . .

ሴትዮዋ ብትጎዳ የጎዳትም ሰው በተመሳሳይ መልኩ መጎዳት አለበት። አማራጭ ትርጉም፦ ሰውዬው ለሕይወቷ ሕይወቱን፥ ለዓይኗ ዓይኑን መክፈል ወይም መጎዳት አለበት