887 B
887 B
• ታምሞ በአልጋው ላይ ቢተኛ
የተመታው ሰው ታሞ በአልጋ ላይ ቢውል ወይም አልጋ ላይ ተኝቶ ቢቀር
• ተነሥቶም በምርኩዝ
በኋላም ተነስቶ ወይም ህመሙ ሲሻለው ወይም በትር እየተመረኰዘ መራመድ ቢችል
• ምርኩዝ
ከእንጨት ወይም ከብረት የተሰራ የጉዞ መደገፊያ
• ተግባሩን ስላስፈታው
ሰውዬው በመታመሙ ምክንያት የባከነውን የሥራ ጊዜ ወይም ሥራ ያልሰራበትን ቀናት የሚመለከት ነው።አማራጭ ትርጉም፦ ሥራ ሳይሰራ ከንቱ ያሳለፈው ጊዜ
• ገንዘብ ይከፍለው ዘንድ
“የመታው ሰው ካሣ ይክፈለው” ወይም “የመታው ሰው የህክምና ወጪ ሊከፍለው ይገባል”