969 B
969 B
• ሰው ሰውን ቢመታ
ሰው ሰውን ቢገድል ወይም ሰውን ደብድቦ የሚገድል
• እርሱ ፈጽሞ ይገደል
ይህንን ተደራጊ ግስ በአድራጊ ግስ መተርጎም ይቻላል፦ ይህን ሰው በርግጥ መግደል አለብህ ወይም ይህ ሰው መሞት አለበት
• ባይሸምቅበትም
ሆን ብሎ ደፈጣ በማድረግ ሳይሆን ወይም ጉዳት ለማድረስ በልቡ ባያስብ ወይም ባያቅድ
• የሚሸሽበት ስፍራ እኔ አደርግልሃለሁ
ሸሽቶ በማምለጥ በሰላም የሚኖርበትን ስፍራ እኔ አዘጋጅለታለሁ
• ባልጀራውን በተንኮል ቢገድለው
ሆን ብሎ ወይም አውቆ ሌላ ሰው ቢገድል
• እንዲሞት ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው
ሕይወቱን ለማዳን ወደ መሠዊያዬ ሸሽቶ ቢሄድ በሞት ይቀጣ