am_tn/exo/19/19.md

911 B

• የቀንደ መለከቱም ድምፅ እጅግ በበረታና በጸና ጊዜ

የእምቢልታው ወይም የጥሩንባው ድምጽ እየበረታ ወይም እያየለ በመጣ ጊዜ

• እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት (ወካይ ዘይቤ)

እዚህ ቦታ “ድምጽ” እግዚአብሔር የሚያሰማውን ድምጽ የሚመለከት ነው። የዚህ ሀረግ ፍቺው 1) እንደ መብረቅ እግዚአብሔር በትልቅ ድምጽ ተናግሯል 2) መብረቅ ድምጽ እንዲያወጣ በማድረግ 3) እግዚአብሔር ራሱ በከፍተኛ ድምጽ ተናገረ

• ሙሴን ወደ ተራራው ራስ ጠራው

ሙሴ ተራራው ላይ እንዲወጣ ጠየቀው/አዘዘው/

• ዳርቻውን እንዳያልፉ

የተወሰነውን ክልል ወይም ድንበር አልፈው እንዳይመጡ