1.8 KiB
1.8 KiB
• የያቆብ ቤት
“የያዕቆብ ቤት” የሚለው የያዕቆብን ቤተሰብ እና ትውልዱን የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ የያዕቆብ ተወላጆች ለሆኑት
• ለያቆብ ቤት . . . ለእስራኤልም ልጆች
“የእስራኤል ልጆች” የሚለው ሀረግ የሚገልጸው “የያዕቆብ ቤት” የሚለውን የሚያብራራ ነው።
• በንስርም ክንፍ እንደ ተሸከምኋችሁ
እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ያደረገውን ጥበቃና ጥንቃቄ ሲገልጽ እርሱ ንስር እንደ ሆነና እነርሱን በክንፉ እንደ ተሸከማቸው አድርጎ ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ ንስር ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ እንደምትሸከም እኔም እናንተን እንዴት እንደተሸከምኳችሁ
• ቃሌን በእውነት ብትሰሙ
“ቃሌን ብትሰሙ” የሚለው እንዲሁ መስማት ብቻ ሳይሆን መታዘዝንም ይጨምራል። በሌላ አገላለጽ፦ ቃሌን ብትሰሙና ለእኔም ብትታዘዙ
• ኪዳኔንም ብትጠብቁ
ቃል ኪዳኔ የምጠይቃችሁን ነገር ብትፈጽሙ
• ርስት ትሆኑልኛላችሁ
የእኔ ርስት ወይም ሀብት ትሆናላችሁ
• የካህናት መንግስት . . . ትሆኑልኛላችሁ (ተለዋጭ ዘይቤ)
እግዚአብሔር ህዝቡ ካህናት እንደሆኑ ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ የመንግስት ህዝብ የሆናችሁ ለእኔ እንደ ካህናት ናችሁ ወይም የመንግስት ህዝብ የሆናችሁ እናንተ ለእኔ ካህናት የሚሰሩትን የምትሰሩ ናችሁ