am_tn/exo/17/01.md

1.3 KiB

• ሲን ምድረ በዳ

“ሲን” የምድረ በዳው ስም ነው፤ (ዘጸአት 16፡1 ተመልከት)

• በራፊዲምም ሰፈሩ

በጉዞ ላይ ሰዎች የሚያርፉበት ወይም የሚቀመጡበት ሥፍራ ነው፤

• ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?

ሙሴ እነዚህን ጥያቄዎች የጠየቃቸው ህዝቡን ለመገሰጽ ወይም ለመኮነን ነው። ይህ አጋናኝ ጥያቄ በመደበኛ ዐረፍተ ነገር ምተርጎምም ይቻላል፤ ከእኔ ጋር ልትጣሉ አይገባችሁም፤ እግዚአብሔርንም (ያህዌን) ልትፈታተኑ አያስፈልጋችሁም

• እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኽን?

እስራኤላውያን ይህንን እአጋናኝ ጥያቄ የጠየቁት በምድረ በዳ ልገድላቸው እንዳመጣቸው አድርገው ሙሴን ለመክሰስ ነው። ይህን አጋናኝ ጥያቄ በመደበኛ ዐረፍተ ነገር መተርጎምም ይቻላል፦ አንተ ከግብጽ ምድር ያወጣኸን እኛን፥ ልጆቻችንን እና ከብቶቻችንን በውሃ ጥም ለመፍጀት ወይም ለመግደል ነው