am_tn/exo/15/06.md

1.5 KiB

• ቀኝህ በኃይል ከበረ

ሙሴ እግዚአብሔር እጅ እንዳለው አድርጎ ይናገራል፤ “ቀኝ እጅ” የእግዚአብሔርን ሀይል ወይም እግዚአብሔር በሀይሉ የሚሰራቸውን ነገሮች ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር ሀይልህ የከበረ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ አንተ በሀይልህ የምትሰራቸው ነገሮች ክቡር ናቸው (ወካይ ዘይቤ)።

• ቀኝህ ጠላቱን አደቀቀ

ሙሴ እግዚአብሔር እጅ እንዳለው አድርጎ ይናገራል፤ “ቀኝ እጅ” የእግዚአብሔርን ሀይል ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር ሆይ ሀይልህ ጠላቶችን አደቀቀ ወይም እግዚአብሔር ሆይ በሀይልህ ጠላቶችን አደቀቅህ

• የተነሡብህን አጠፋህ

በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ በእግዚአብሔር ላይ እንደመነሳት ተቆጥሯል፤ አማራጭ ትርጉም፦ በአንተ ላይ ያመጹ ወይም ጠላቶችህን

• ቍጣህን ሰድደህ

የእግዚአብሔርን ቁጣ ሙሴ ሲገልጽ አንድ ነገር ለመሥራት እንደ ተላከ አገልጋይ አድርጎ ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ ቁጣህን አሳየህ ወይም አንተ እንደ ቁጣ ሥራህን ፈጸምክ

• እንደ ገለባም በላቸው

x