am_tn/exo/15/04.md

950 B

• የፈርዖንን ሰረገሎች ሠራዊቱንም በባሕር ጣላቸው

ሙሴ ስለእግዚአብሔር ሲዘምር እግዚአብሔር ባህሩን በፈርዖን፥ ሰረገሎችና በሠራዊቱ ላይ መመለሱን በባህር ውስጥ እንደመጣል ተነግሯል። አማራጭ ትርጉም፦ እርሱ በፈርዖን ሰረገላዎችንና በሠራዊቱ ላይ ባህሩን መልሷል ወይም እርሱ የፈርዖን ሰረገላዎችንና ሠራዊቱን በባህር አስጥሟል

• ወደ ባሕር ጥልቀት እንደ ድንጋይ ሰጠሙ

ድንጋይ በባህር እስከ ውስጥ እንደሚሰጥም የጠላት ሠራዊት እስከ ባህሩ ጥልቅ ድረስ መስጠማቸውን ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ ድንጋይ በባህር ውስጥ እንደሚሰጥም እነርሱ በብሃር ውስጥ ሰጠሙ (ተነጻጻር ዘይቤ)