am_tn/exo/15/02.md

1.1 KiB

• እግዚአብሔር ጉልበቴ ነው (ወካይ ዘይቤ)

አማራጭ ትርጎሞች፦ 1) ሀይልን የሚሰጠኝ እግዚአብሔር ነው 2) እኔን የሚጠብቀኝ ወይም የሚከላከለኝ እግዚአብሔር ነው

• ዝማሬዬ እግዚአብሔር ነው (ወካይ ዘይቤ)

ሙሴ እግዚአብሔርን የዝማሬዬ ምንጭ ነው ወይም እግዚአብሔር እኔ የሚዘምርለት እርሱ ነው

• መድኃኒቴም ሆነልኝ (ወካይ ዘይቤ)

ሙሴ እግዚአብሔር መድሀኒቴ ብሎ ይጠራዋል ምክንያቱም እርሱ ከግብጻውያን እጅ አድኖአቸዋልና። አማራጭ ትርጉም፦ የሚያድነኝ እግዚአብሔር ነው

• እግዚአብሔር ተዋጊ ነው

ሙሴ እግዚአብሔርን ተዋጊ ብሎ ይጠራል ምክንያቱም እርሱ በሀይሉ ግብጻውያንን ተዋግቶ አሸንፏል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር እንደ ብርቱ ተዋጊ ነው (ተለዋጭ ዘይቤ)