1.1 KiB
1.1 KiB
• በሚመጣው ጊዜ ልጅህ፦ ይህ ምንድር ነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ
በሌላ አገላለጽ፦ “በሚመጡት ዘመናት ልጆችህ የዚህ ሥርዓት ትርጉም ምንድን ነው” ብለው ቢጠይቁህ፥ እንዲህ ብለህ ታስረዳቸዋለህ
• እግዚአብሔር በብርቱ እጅ
ምክንያቱም እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ
• የባርነት ቤት
ህዝቡ በአንድ ቤት ታጉሮ እንደነበር ዓይነት አነጋገር የያዘ ዘይቤ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “በባርነት የነበራችሁበትን ሁኔታ ወይም ሕይወት”
• በእጅህ እንደ ምልክት፥ በዓይኖችህም መካከል እንደ ተንጠለጠለ ነገር ይሁንልህ
እስራኤላውያን በዓሉን ወይም የፋሲካ በዓል ሲያከብሩ እነዚህን ሁለት የሚታዩ ምልክቶችን እንድያደርጉ ሙሴ ያሳስባቸዋል (ተነጻጻሪ ዘይቤ፤ ለተመሳሳይ አገላለጽ 13፡8-10 ተመልከት)