am_tn/exo/13/08.md

1.8 KiB

• በዚያም ቀን፦ ከግብፅ በወጣሁ ጊዜ እግዚአብሔር ስላደረገልኝ ነው ስትል ለልጅህ ትነግረዋለህ

ይህ አነጋገር በቀጥታ አነጋገር ሲገለጽ፦ “በዓሉን በምታከብርበት ወቅት ይህን የምታደርገው ከግብጽ በወጣህበት ጊዜ እግዚአብሔር ያደረገልህን መልካም ነገር ለማስታወስ መሆኑን ለልጆችህ ንገራቸው”

• በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶሃልና

ምክንያቱም እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ አውጥቷችኋል

• በእጅህ እንደ ምልክት በዓይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ

እስራኤላውያን በዓሉን ወይም የፋሲካን በዓል ሲያከብሩ እነዚህን ሁለት የሚታዩ ምልክቶችን እንድያደርጉ ሙሴ ያሳስባቸዋል።

• በእጅህ እንደ ምልክት

ሙሴ ሲናገር እስራኤላውያን በዓሉን ሲያከብሩ በእጃቸው የሆነ ነገር አስረው እንደምያከብሩ አድርጎ ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ ለምልከነት በእጅህ ላይ የሆነ ነገር እንደምታስረው ይሁን።

• በዓይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ

ሙሴ ሲናገር እስራኤላውያን በዓሉን ሲያከብሩ በግንባራቸው የሆነ ነገር አስረው እንደምያከብሩ አድርጎ ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ ለምልክትነት በግንባርህ ላይ የሆነ ነገር እንደምታስረው ይሁን።

• በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶሃልና

ምክንያቱም እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ አውጥቷችኋል