928 B
928 B
• የእስራኤልም ልጆች በግብፅ ምድር የተቀመጡት ዘመን አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው
እስራኤላውያን በግብጽ ምድር የኖሩት አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር
• የእግዚአብሔር ሠራዊት ሁሉ ከግብፅ ምድር ወጣ
እዚህ ጋር ሠራዊት የተባለው የእስራኤልን ህዝብ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ የግብጽን ምድር ለቆ ወጣ” (ዘጸአት 12፡17 ተመልከት)
• በእስራኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ እስከ ልጅ ልጃቸው ድረስ ለእግዚአብሔር የተጠበቀች ናት
ይህ ሌሊት እስራኤላውያን በመጠባበቅ ተግተው የሚያድሩበትና ለሚመጣው ትውልድ ወይም ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሌሊት ነው