am_tn/exo/12/37.md

1007 B

• ከራምሴ

ራምሴ ግብጻውያን እህል ከሚያከማቹባቸው ከተሞች አንዱ ነው። (ዘጸአት 1፡11 ተመልከት)

• ከሕፃናቱም ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህል እግረኛ ነበረ

“ህጻናት” የተባሉት ድጋፍ የሚፈልጉ ወንድና ሴት ልጆችን የሚመለከት ወይም ህጻናትና ሴቶችን የሚመለከት ሊሆን ይችላል። ጠቅላላ መዋጋት የሚችሉ ወንዶች ብዛት ስድስት መቶ ሺህ ያህል ነበር።

• ከግብፅም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ጋገሩ

ከግብፅ ይዘው ከወጡት ሊጥ ያልቦካ ቂጣ ጋገሩ

• ግብፃውያን በመውጣት ስላስቸኮሉአቸው ይቆዩ ዘንድ አልተቻላቸውም

ከግብፅ በጥድፊያ ወይም በችኮላ እንዲወጡ ስለተደረጉ ለራሳቸው ምግብ ለማዘጋጀት ጊዜ አልነበራቸውም