am_tn/exo/12/17.md

1.1 KiB

• ሠራዊታችሁን ከግብፅ አገር አውጥቼአለሁና

ይህ አገላለጽ ለጦር ሠራዊት የተሰጠ ስም ሲሆን በዚህ ክፍል የተገለጸው “ክፍል ለክፍል ወይም ቡድን ለቡድን” በሰልፍ የሚወጣውን የእስራኤልን ህዝብ የሚመለከት ነው።

• ሲመሽ

“ምሽት” የሚለው ቃል ሙሉ በሙሉ ሲመሽ ሳይሆን ፀሐይ መጥለቂያ እና ማምሻ መካከል ያለው ሰዓት ሲሆን ከመጨለሙ በፊት ብርሃን ያለ ማለት ነው።

• በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን

ይህ ወር በእስራኤላውያን ዘመን አቆጣጠር የአመቱ የመጀመሪያ ወር ነው። በአውሮጳውያን አቆጣጠር የመጋቢት መጨረሻ ሳምንት እና የሚያዚያ የመጀመሪያ ሳምንት አከባቢ የሚጀምር ወር ነው።

• ከወሩም እስከ ሀያ አንድ ቀን በመሸ ጊዜ

የመጀመሪያ ወር በገባ በ21ኛው ቀን ማለት ነው