am_tn/exo/12/15.md

1.1 KiB

• ማንኛውም ሰው ከእስራኤል ይጥፋ

“ይጥፋ” የሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ሶስት አማራጭ ፍቾች ይኖሩታል። 1) የእስራኤል ሰዎች ይህን ሰው ከመካከላቸው አውጥተው ማስወገድ አለባቸው 2) ይህ ሰው ከእስራኤላውያን እንደ አንዱ መታየት የለበትም 3) እስራኤላውያን ይህን ሰው መግደል ወይም ማጥፋት አለባቸው።

• በመጀመሪያውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ እንዲሁም በሰባተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንላችኋል

በመጀመሪያውና በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ

• ከሚበላ በቀር በእነርሱም ምንም አትሠሩም

በእነዚያም ቀኖች ምግባችሁን ከማዘጋጀት በቀር ምንም ሥራ አትሠሩም

• ይህንም ብቻ ታደርጉታላችሁ

የምትሠሩት ሥራ ቢኖር ለእያንዳንዱ ምግብ ማዘጋጀት ብቻ ይሆናል።