am_tn/exo/07/03.md

1.3 KiB

• እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ

“ልብ” ተብሎ በወካይ ዘይቤ የተገለጠው ራሱን ፈርዖንን ለመግለጽ ነው። የፈርዖንን ልብ ያደነደነው እግዚአብሔር ራሱ እንደሆነ ልብ ይሏል። ስለሆነም ልቡን እግዚአብሔር ስላደነደነው ፈርዖን ለመስማት አልፈለገም ወይም እምብተኛ ሆነ ማለት ነው። (ምዕራፍ 3፡21 ተመልከት)

• ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ

“ድንቅና ታአምር” ሁለቱም ተመሳሳይ ወይም ቅርብ ፍቺ ያላችው ቃላት ናቸው። ታአምር ድርጊቱን ወይም ክስተቱን ሲገልጽ ድንቅ ምልክትን ወይም የክስተቱ ማረጋገጫ የሚመለከት ነው። ሁለቱም ከተፈጥሮ ክስተት ውጪ የሆኑ የእግዚአብሔር አሰራሮች ናቸው።

• እጄንም በግብፅ ላይ አደርጋለሁ

“እጄን” ሲል ለፍርድና ለቅጣት የተዘረጋውን የእግዚአብሔር እጅ እንጂ የማደፋፈር ወይም የማነቃቃት እጅ ማለት አይደለም። አማራጭ ትርጉም፦ ግብጻውያንን በመፍረድ ወይም በመቅጣት ታላቁን ሀይሌን አሳያቸዋለሁ”