• እግዚአብሔርም አሮንን
በዚህ ክፍል የታሪኩን አዲስ ጀማሮ ለማመልከት የሚረዳ አንድ አገናኝ ቃል መጠቀም ጥሩ ነው። ለምሳሌ፦ “በዚህን ጊዜ” ብሎ መቀጠል ይቻላል።
• በእግዚአብሔር ተራራ ተገናኘው
ይህ በሲና የሚገኘው ተራራ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በትክክል የትኛው ተራራ እንደሆነ አይናገርም።
• እግዚአብሔር በእርሱ ዘንድ የላከውን ቃል ሁሉ
በእርሱ ዘንድ የሚለው ቃል በሙሴ በኩል የሚለውን ፍቺ ይይዛል።