am_tn/exo/04/24.md

1.6 KiB

• በመንገድ ላይ ባደረበት ስፍራ እግዚአብሔር ተገናኘው፥ ሊገድለውም ፈለገ

የዚህ ትርጉም በትክክል ባይታወቅም ምናልባት ሙሴ ልጁን ባለመገረዙ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

• ሲፓራም ሚስቱ

የሙሴ ሚስት ስሟ ሲፖራ ወይም በዕብራይስጡ ጽፖራ ነው።

• ባልጩት

የተፈጥሮ ስለት ያለው ለመቁረጥ የሚያገለግል የባልጩት ድንጋይ

• ወደ እግሩም ጣለችው

ይህ “ወደ እግሩም ጣለችው” የሚለው ሀረግ ሁለት ዋና ዋና የትርጉም አመለካከቶች አሉት። 1) ልጁ መገረዙን ለማመልከት በእግሩ ላይ የደም ምልክት እንድኖር ስትፈልግ እናቱ የቆረጠችውን ሸለፈት በልጁ እግር ላይ መጣሏን፤ 2) “እግር” የሚለው ቃል በእስራኤላውያን ዘንድ የአይነኬ ዘይቤ አገላለጽ በመሆኑ ወደ ሙሴ የመዋለጃ ብልት ላይ ጣለችው የሚል አመለካከትም አለው።

• አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ነህ

የዚህ ሀረግ ፍቺው ወይም መልዕክት ግልጽ አይደለም። እንደዚህ ዓይነት ንግግር በጊዜው በእስራኤል ታሪክ የሚታወቅ ልሆን ይችላል። አማራጭ ትርጉም፦ “በዚህ ደም ምክንያት አንተ ከእኔ ጋር ግንኙነት አለ” ወይም “በዚህ ደም ምክንያት አንተ ለእኔ ባሌ ነህ”