am_tn/exo/04/10.md

2.0 KiB

• አፌ ኮልታፋ

ደህና አድርጎ መናገር የማይችል ወይም አንደበቴ ርቱዕ ያልሆነ ሰው ማለት ነው

• ምላሴም ጸያፍ የሆነ ሰው ነኝ

አንደበቱ የሚኮላተፍና አጥርቶ መናገር የማይችል ሰው ማለት ነው። ሙሴ ይህን የተናገረው አጥርቶ መናገር የማይችል ሰው መሆኑን ለመግለጽ ሲፈልግ ነው።

• ምላሴም ጸያፍ

ኮልታፋና ተናግሮ ለማሳመን አቅም የሚያንሰው መሆኑን ያሳያል (ምትካዊ ዘይቤ)

• የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው?

እግዚአብሔር (ያህዌ) ይህን ጥያቄ ሲጠይቅ ሰዎች መናገር እንዲችሉ አድርጎ የፈጠረውና ለመናገርም አፍ የፈጠረው እርሱ ራሱ መሆኑን ለማጽናት ፈልጎ ነው (አጋናኝ ዘይቤ)

• ዲዳስ ደንቆሮስ የሚያይስ ዕውርስ ያደረገ ማን ነው?

እግዚአብሔር (ያህዌ) ይህን ጥያቄ የጠየቀው ሰዎች መናገርና መስማት እንዲችሉ የሚያደርገው ራሱ እንደሆነ ለማሳየት ነው (አጋናኝ ጥያቄ)

• እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?

እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ ሲጠይቅ ሁሉን ነገር የሚወስነው ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ለማጽናት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? (አጋናኝ ጥያቄ) ወይም ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

• እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ

“አፍ” የሚለው ቃል የሙሴ የመናገር ችሎታውን ለማሳየት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “የመናገር ችሎታ ለአንተ እሰጣለሁኝ” ወይም “መናገር እንድትችል አደርጋለሁ”