879 B
879 B
• አለቀሱ
ከመከራቸውና ከጭንቃቸው የተነሳ ማልቀሳቸውን የሚያሳይ ነው
• ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ
የእስራኤላውያን ጩኸት እግር እንዳለው ሰው ወደ እግዚአብሔር እንደተጓዘ ወይም እንደሄደ በሰውኛ ዘይቤ የተነገረ ነው። በቀጥተኛ ዐረፍተ ነገር ሲነገር “እግዚአብሔር ጩኸታቸውን ሰማ” የሚል ነው።
• እግዚአብሔር . . . ቃል ኪዳኑን አሰበ
ይህ አባባል በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ ነው። ሰው አንድን ነገር ረስቶ እንደገና እንደሚያስብ የተነገረ ዘይቤያዊ ንግግር ነው። በሌላ አገላለጽ፦ “እግዚአብሔር የገባውን ቃል ኪዳን አሰበ”።