am_tn/exo/02/15.md

1.4 KiB

• ፈርዖንም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ

በታሪኩ ውስጥ ፀሐፊው ሌላ ሀሳብ ሲያስገባ ወይም አዲስ የታሪክ ክፍል ሲጨምር እንመለከታለን። ሙሴ ያደርገውን ነገር ፈርዖን ሰምቶታል ማለት ነው ወይም ወሬው ወደ ፈርዖን ደረሰ ማለት ነው።

• ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት

ጸሐፊው በታሪኩ ውስጥ አዳዲስ ሰዎችን ወይም ተዋንያንን ሲጨምር እናያለን፥

• እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ

በጊዜው ዕብራውያን ውሃ የሚቀዱት ከጉድጓድ ነበርና ውሃ ለመቅዳት ወደ ጉድጓዱ እንደመጡ ያሳያል።

• ገንዳ

ከእንጨት ወይም ከድንጋይ ወይም ከሌሎች ነገሮች የሚሰራ ከብቶችን ውሃ ለማጠጣት ወይም መኖ ለመስጠት የሚያገለግል ነው።

• እረኞችም መጥተው ገፉአቸው

እረኞችም መጥተው እነዚያን ሴቶች አባረሩአቸው፥ ከለከሉአቸው፥ አሳደዱአቸው እንደማለት ነው።

• ሙሴ ግን ተነሥቶ ረዳቸው

እረኞችም መጥተው ሴቶቹን ሲያባርሯቸው ሙሴ ከተቀመጠበት ተነሥቶ ተከላከለላቸው፥ ከእረኞችም እጅ አዳናቸው ወይም አስጣላቸው ማለት ነው።